መጋቢት 11/2014 ዓ.ም  

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር ዉይይት አደረጉ፤ 

የዉይይቱን መድረክ የከፈቱት  የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጰጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ የዉይይቱ ማስጀመሪያ  እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዉ  አጠቃላይ ስለ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች የሚያስቃኝ ሰነድ ለተሳታፊዎች አቅርበዋሉ፡፡ 

ዉይይቱ  የሀገርቱን የትምህርት ሥርዓት በጋራ ዕይታ እና መግባባት መምራት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ ነዉ፡፡ 

የትምህርት ሥርዓቱ ዙሪያ ያሉ ችግሮች ዙሪያ የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ ጥያቄዎችን አንስተዉ በትምህርት  ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ፤በከፍተኛ ትምህርት  ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እና በትምህርት  ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ  ምላሽእና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ 

ሚኒስቴሩ አክለዉም የትምህርት ተቋማት ነፃ እና ገለልተኛ ሆነዉ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በፍታዊነት እና በእኩልነት ማገልገል እንዳለባቸዉ እና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሁሉም በጋራ መስራት እንዳለበት ገልጸዋሉ፡፡ 

 በዉይይቱ የትምህርት ሚንስቴር የሥራ አመራሮች ፤የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፤ዳይሬክተሮች፤ ኮሌጅ ዲኖች እና ም/ዲኖች፤የት/ት ክፍል ኃላፊዎች፤መምህራን እና የቡዲን መሪ አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል፡፡