ዩኒቨርሲቲው በ2010 ዓ/ም በካፋ ዞን ከጨና ወረዳ ለተፈናቀሉ 517 የህብረተሰብ ክፍሎች 80 ፍራሽ፣ 100 ባለ 20ሊትር የውሃ መቅጃ ጀርካንና 50 የመመገቢያ ሰሃኖችን አበርክቷል፡፡ እንደዚሁም በ2011 ዓ/ም በሸካ ዞን የኪ ወረዳ - ቴፒ ከተማ በተቀሰቀሰው ግጭት ከቤት ንብረታቸው በመፈናቀል በቴፒና ማሻ ከተማ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ተጠልለው ለሚገኙ ወገኖች 200 ኩንታል የስንዴ ዱቄትና 1000 ሊትር የምግብ ዘይት ግዥ በመፈፀም ድጋፍ አድርጓል፡፡


በ2010 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በደቡብ ክልል ጉጂ ዞን የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሄደው በተመለከቱት አጋጣሚ ህፃናትን ጨምሮ ከ763ሺህ በላይ የሆኑ ተፈናቃዮች በገደብ ወረዳ በረሃብ፣ ጥማትና እርዛት ምከንያት እጅግ አሳቃቂና አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ መኖራቸውን በማየት ዩኒቨርሲቲው ካለው ውስን ሀብት 200 ፍራሽ፣ 300 ባለ 32 ጌጅ ቆርቆሮ፣ 250 ባለ 20ሊትር የውሃ መቅጃ ጀርካን፣ 150 የመመገቢያ ሰሃኖችን እስከ ቦታው ድረስ በመውሰድ ለግሷል፡፡

በሁለተኛው ዙር በጉጂ ዞን ገደብ ወረዳ  በ2011 ዓ/ም 200 ኩንታል የፉርኖ፣ የሽሮና በርበሬ ዱቄት እና 300 ቆርቆሮ ጭኖ በመውሰድ ሀገራዊና ሰብዓዊ ገዴታውን ተወጥቷል፡፡


በአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው ከጉጂ፣ ከፋና ሸካ ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ891,000 ብር በላይ የሚገመቱ ቁሳቁሶችን በራሱ የትራንስፖርት ወጪ እቦታው ድረስ በመውሰድ አበርክተዋል፡፡

2013 በጀት ዓመትም በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቃሉ ወገኞች 30 ኩንታል ጤፍ፣ 30 ኩንታል ሩዝ፣ 10 ኩንታል ስኳር፣ 200 ቆርቆሮና 3000 ሳሙና ድጋፍ አድርጓል፡፡ 


በ2014 ዓ/ም/ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለደባርቅ ሆስፒታል ከሰላም ማስከበሩ ስራ ጋር ተያይዞ ለሚከሰተው ጉዳት ሆስፒታሉ በሙሉ አቅሙ እንዲሰራ ለማድረግ በሀገሪቱ ለሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የድጋፍ ጥሪውን ባስተላለፈው መሠረት ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ስድስት መቶ ሺህ ብር በሚጠጋ ገንዘብ 200 ፍራሽ፣ 100 የሌሊት ልብሰ /Sleeping Bag / እና 19 የአካል ጉዳተኞች መንቀሳቀሻ /Willcher/ ገዝቶ በመለገስ ለሀገር መከላከያ እና ለአማራ ልዩ ኃይል ያለውን አለኝታነት በግንባር ቀደምትነት ያሰየ ሲሆን የተደረገውንም ድጋፍ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲን በመወከል ለደባርቅ ሆስፒታል እንዲያስረክብ በማድረግ አጋርነቱን ገልጿል፡፡ 




ሀገራዊ ህልውናን ለማስከበር በተደረገው ዘመቻ ምክንያት ደሴ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖቻችን 2000 ሊትር ፈሳሽ ሳሙና /ላርጎ/፣ 1000 የገላ ሳሙና፣ 2000 አጃክስ ሳሙና፣ 50 ብርድ ልብስ እና 200 ፍራሽ በወሎ ዩኒቨርሲቲ በኩል እንዲደርስ ዩኒቨርሲቲው እስከ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ድረስ በመውሰድ በስጦታ አበርክቷል፡፡ 

 

በምር/ማህ/አገ/ም/ፕሬዝዳንት የተመራው ቡድን ሀገራዊ ህልውናን ለማስከበር ደሴ ለሚገኙ ወገኖች ከዩኒቨርሲቲው የሄዱ ቁሳቁሶችን ቦታው ድረስ በማድረስሲያስረከቡ

በተጨማሪም በደብረ-ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች 200 ኩንታል ሩዝ፣ 400 ሊትር ላርጎ ፈሳሽ ሳሙና እና 100 አንሶላና ብርድ ልብስ እስከ ደበረ-ብርሃን ዩኒቨርሲቲድረስ በማድረስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የምር/ማህ/አገልግሎት እና የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝዳንቶ  በዩኒቨርሲቲው የተዘጋጀውን ድጋፍ ለተወካዮች ሲያስረክቡ

Odoo • Image and Text

Dr.Solomon 

Director for Community Services    

Cell Phone : +2519

Office phone  

P.O.Box   :334

Email :    

Full Address of the Office : Admin Building 4 st  floor Office   No.AD 408