Odoo • Image and Text
Odoo • Image and Text
Odoo • Image and Text
Odoo • Image and Text

ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና  ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተላቸው።


ቦንጋ ዩኒቨርስቲ በካፋ ዞን ውስጥ ከሚገኙ የመሰናዶ ት/ት ቤቶች የ2015 የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና  ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተላቸው።

በመርሀ-ግብሩ በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን የመክፈቻ ንግግር በዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ   ተደርጓል፡፡ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት የሕይወት  ተሞክሯቸዉን አካፍለዉ  ተማሪዎቹ በቀጣይ ዩኒቨርሲቲ በሚኖራቸዉ  ቆይታ ተግተዉ በመሥራት ራሳቸዉንና ቤቴሰቦቻቸዉን ከመርዳት ባለፈ ለሀገር ሁለንተናዊ ለዉጥ የየራሳቸዉን ድርሻ እንድወጡ የቃል ኪዳን መሀላ አስፈጽመዋል፡፡

በሽልማት መርሀግብር ላይ  ሁሉም የካፋ ዞን  ዉስጥ ያሉ የመሰናዶ ት/ት ቤቶች ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፤

1. በመጀመሪያ ተማሪ ቢንያም ማርቆስ  ከዴቻ ወረዳ አዉራዳ ት/ት ቤት በተፈጥሮ ሳይንስ 602 ዉጤት በማስመዝገብ   የ30 ሺህ (30,000) ብር የገንዘብ ሽልማትና  core  i7 የላፕቶፕ ተሸላሚ ሲሆን 

2 ለ19 (አስራ ዘጠኝ)  ተማሪዎች የcore I 7 የላፕቶፕ ሽልማት ተበርክተዋል፡፡

በተያያዘም በትምህርት ዘርፍ በተመዘገበዉ ዉጤት ዙሪያ  ዉይይት ተደርጓል፡፡ በዉይይቱ ላይ የካፋ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፤ የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች፣ የካፋ ዞን ካቢኔዎችና የት/ት ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣የሀገር ሽማግለዎች  ተሳትፈዋል፡፡

መድረኩን የመዝግያ ንግግር ያደረጉት የካፋ ዞን ም/አስተዳዳሪ አቶ ደመላሽ ንጉሴ ዩኒቨርሲቲዉ በግብርና፣በጤና፣በትምህርት፣በባህልና ቱሪዝም  ላይ  በርከት ያሉ ስራዎችን እየሰራ የራሱን አሻራ እያስቀመጠ መሆኑን በመጥቀስ ለተማሪዎቻችን ለተሰጠዉ እዉቅና ምስጋና አቅርበዋል፡፡በቀጣይም በትምህርት ጥራት ላይ ከKG  ጀምሮ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል፡፡