Odoo • Image and Text

የካቲት 29//2014 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበሌ የተመራ ልዑክ እና በሚኒስቴር ደኤታ ማዕረግ የግብርና ሚኒስቴር የሚኒስትሩ ፖሊሲ አማካሪ  አቶ እፋ ሙሌታ  የተመራ ልዑክ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እየተከናወኑ ያሉ ልማታዊ ሥራዎችን ጎበኝተዋል።

በጉብኝታቸዉ የተለያዩ የቡና፣ ሻይ ቅጠል፣ አቮካዶ ፣ማንጎ ፣ሙዝ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን የዛፍ፣ የቅመማ ቅመምና የመድሃኒት ተክሎች የግቢው ውበትና ገፀ- በረከቶች መሆናቸውን ዘርፉን የሚመሩ የዩኒቨርሲቲዉ ም/ፕሬዝዳቶች  ለልዑካኑ ገለፃ አድርገዋሉ። ዳይሬክተሩ በተቋሙ ቡና፤ የቅመማ ቅመምና የመድሃኒት ተክሎች ላይ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር በመሆን ዓለም አቀፋዊ ትስስር ለማድረግ እንደሚሰራም ቃል ገብተዋል። ሚንስትር ደኤታዉ አክለዉም ዩኒቨርሲቲዉ በአካባቢ ጥበቃና በማህበረሰብ አገልግሎት እያከናወነ ያለው ተግባር እጅግ የሚደነቅና ኋላ ቀር የግብርና ስራን ለማስቀረት አይነተኛ ሚና ያለው  መሆኑን በመግለፅ ዘመናዊ ግብርናን ለማስፋፋት ከሚንስቴር መ/ቤቱ ጋር በጋራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

 

Odoo • Image and Text
Odoo • Image and Text
Odoo • Image and Text
Odoo • Image and Text