የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በቡና ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ለመስጠት የመጨረሻ ካሪኩሌም ሪቪዉ( External Curriculum Review) ታህሳስ 16 ፣ 2014 ዓ.ም  አካህዷል ፡፡

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በቡና ሳይንስ (Coffee Science) የመጀመሪያ ዲግሪ ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በቡና ምርት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመመራመር ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን በሚያስችለው የቡና ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ አጀማመር ላይ የመጨረሻው ውይይት የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ተመራማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት / ጴጥሮስ / ጊዮርጊስ የቡና መገኛ በሆነችው ኢትዮጵያ እንደ ትምህርት አለመሰጠቱ አሳዛኝ ሆኖ ቢዘልቅም ዛሬ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመር መወሰኑ በቡና ተጠቃሚነት ላይ ታሪክ ሆኖ የሚነገር ይሆናል ብለዋል።
ኢትዮጵያ 83 በመቶ በላይ ህይወታቸውን በግብርና የሚመሩ ዜጎች ሀገር በመሆኗ ከጥገኝነት ለመላቀቅ ዛሬ በቡና ነገ ደግሞ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በእንሰት ላይ መስራት አለብን ብለዋል።

በዓለማችን በቀን አንድ ቢሊየን ያህል ሰዎች ቡናን የሚጠቀሙ ስለመሆኑ በመድረኩ የተጠቀሰ ሲሆን ይህን ትልቅ ሀብት በትምህርትና ምርምር አስደግፎ መምራት የሀገራዊ ለውጥ አካል ሆኖ በትኩረት መያዝ አለበት ተብሏል።

በመድረኩ ለትምህርት ዘርፉ ውጤታማነት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ምስጋና የቀረበ ሲሆን በቀጣይም ባለድርሻ አካላት በትኩረት እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።