ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የ 2014 ዓ . ም የመጀመሪያ የ 6 ወር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ጥር 13/2014 ዓ.ም አካህዷል፡፡
የ 6 ወራት የሥራ እቅድ አፈጻጸሙን የመሩት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ / ር ጴጥሮስ ወ / ጊዮርጊስ ሲሆኑ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም / ፕሬዝዳንት ጽ / ቤት ዘርፍ ፤የአካዳሚክ ጉዳዮች ም / ፕሬዝዳንት ጽ / ቤት ዘርፍ ፣ የቢዝነስ እና ልማት አገልግሎት ም / ፕሬዝዳንት ጽ / ቤት ዘርፍ ፣ የአስተዳደር እና የተማሪዎች አገልግሎት ም / ፕሬዝዳንት ጽ / ቤት ዘርፍ ፣ የስትራቴጅክ አጋርነት እና የዉጭ ግንኙነት ም / ፕ / ጽ / ቤት ዘርፍ ዉስጥ ያሉ ዳይሬክተሮች፣ኮሌጅ ዲኖች፤ምክትል ዲኖች፤ት / ት ክፍል ኃላፊዎች የተገኙበት ሲሆን በሁሉም ዘርፎች የተጠናከረ ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተደርጓል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለዉም ለቀጣይ ስድስት ወራት ዕቅድ ላይ ለሁሉም የሥራ ዘርፎች አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡