Odoo • Image and Text

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ   ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት 15  ሚሊዮን ብር እና 30  ሰንጋ ድጋፍ   አደረገ።

የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት / ጴጥሮስ / ጊዮርጊስ   በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተደረገውን ድጋፍ ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም የሀገር ህልውና ለማስከበር ግዳጅ ላይ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት በአይነት 15 ሰንጋ ማበርከቱን እና ከሰሜን የሀገርቱ ክፍል ከቀያቸዉ ተፈናቅለዉ ደሴ፤ደብረታቦር   ከተማ   ተጠልለዉ ለነበሩ ተፈናቃዮች   አልጋ ፍራሽ እና የተለያዩ የንጽህና መጠባበቅያ ድጋፍ ማድረጉን እና አጋርነት ማሳየቱን ገልፀው ዛሬ ደግሞ ከዩኒቨርሲቲ   ማህበረሰብ 15 ሚሊዮን ብር እና በአይነት 30 ሰንጋ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
በተጨማሪም በሁለተኛው ዙር እንደዚሁ በዩኒቨርሲቲው እየደለቡ ካሉ በሬዎች መካከል በ1,200,000 የሚገመቱ 30 በሬዎችን እና በጥሬ ገንዘብ የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ  አክለው እንደገለጹት የማህበረሰብ አገልግሎት ተልዕኮን የምናሳካው ሀገር ስትኖር ብቻ መሆኑን እና ሀገራችንን አያየን አሳልፈን አንሰጥም! ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ብለዋል፡፡ አያይዘውም ፕሬዝዳንቱ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰቡ ለመከላከያ ሠራዊት ደጀንነቱን በማሳየት ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ወደፊትም ይህ ተግባር የሚቀጥል መሆኑን ጠቅሰዋል።

በጋራ እንችላለን !!

Odoo • Image and Text

በማዕድማጋራትፕሮግራምላይ እንግዶችን ሲያስተናግዱ

Odoo • Image and Text

በማዕድማጋራትፕሮግራምላይ እንግዶችን ሲያስተናግዱ

Odoo • Image and Text

 

የዩኒቨርሲቲውፕሬዝዳንት በማዕድማጋራትፕሮግራምላይ እንግዶችን ሲያስተናግዱ

እንደዚሁም በከተማውና በዩኒቨርሲቲው ዙርያ ለሚገኙ 450 አረጋዊያንና የኢኮኖሚ አቅም ዉስንነት ላለባቸዉ የማህበረሰብ ክፍሎች በሦስት ማዕከል የማዕድ ማጋራት ሥራና ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስች የእጅ መታጠቢያ ሳሙናና የአፍአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ የመስጠት ተግባርም ተከናዉኗል፡፡

Odoo • Image and Text

ለአቅመ ደካማ አረጋዊያን የምግብ ዱቄት ሲሰጣቸው በከፊ

በሌላ መልኩም ኮሮና /ኮቪድ-19/ ቫይረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፍጥነትና በስፋት በመዛመት በሀገር ኢኮኖሚና በማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ ያሳደረውን አሉታዊ ተጽዕኖ ከግምት በማስገባት ዩኒቨርሲቲው እንደጋገፋለን፤ይህንን ክፉ ጊዜ ተያይዘን እንሻገራለን !” በሚል መሪ ቃል ዛሬም ወረርሽኙ በማህበረሰቡ ላይ ባስከተለው የኑሮ ቀውስ ምክንያት በኑሯቸው ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ በውል በመረዳት ዩኒቨርሲቲው በዞኑ ባሉ 11 ወረዳዎችና 2 የከተማ አስ / ሥር ካሉ ነዋሪዎች መካከል ሰርተው የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን ያልቻሉ ግለሰቦች በወረዳው አማካይነት ተለይተው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ለ እያንዳንዱ ወረዳ ካለው የተረጂዎች ቁጥር ብዛት አንፃር 28 እስከ 600 ኩንታል በድምሩ 995 ኩንታል የምግብ እህል እና 100 ሊትር የንፅህና መጠበቂያ ፈሳሽ ሳሙናና በቁጥር 150 ባለ 100 ሚሊ ሳኒታይዘር እንዲሁም በአይነትና በመጠን በርካታ የምግብ መሥሪያ ቁሳቁሶች ተደራሽ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል፡፡

Odoo • Image and Text

በዩኒቨርሲቲው ስለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ስቱዲዮ በዩኒቨርሲቲው የኮሮና ቫይረስ ግንዛቤ አስጨባጭ ኮሚቴ መልዕክት ሲተላለፍ

Odoo • Image and Text

ፕሬዝዳንቱ : 
ም/ፕሬዝዳንቶች: ዲኖች : ዳይሬክተሮችና የት/ት ክፍሎች የመስክ ጉብኝት ግቢው ውስጥ ካደረጉ በኃላ ውይይት አድርገዋል! ጠቃሚ ግብዐትም ተገኝቶበታል!
በጋራ እንችላለን

Odoo • Image and Text
Assiduously continued to Gawata, Gesha and Saylem together with chief Adminstrator of Kafa zone for usual awarness creation and Support
Odoo • Image and Text

 

ለአቅመ ደካማ አረጋዊያን የምግብ ዱቄት ሲሰጣቸው በከፊል
=====================================

እንደዚሁም በከተማውና በዩኒቨርሲቲው ዙርያ ለሚገኙ 450 አረጋዊያንና የኢኮኖሚ አቅም ዉስንነት ላለባቸዉ የማህበረሰብ ክፍሎች በሦስት ማዕከል የማዕድ ማጋራት ሥራና ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስች የእጅ መታጠቢያ ሳሙናና የአፍአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ የመስጠት ተግባርም ተከናዉኗል፡