የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ደኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የተመራ ልዑክ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲን ጥር 08/2014 ዓ.ም ጎበኙ::
የ
ጤና ሚኒስትር ሚኒስቴር ደኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የተመራ ልዑክ ፤የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም / ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አስቻለው አባይነህ ፤ ጤና አጋር ድርጅቶች እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዬጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች ቦንጋ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ።
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል:: የዩኒቨርሲቲዉን አጠቃላይ እንቅስቃሴን በሚመለከት የዩኒቨርስቲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ዳይሬክቴሮች ገለጻና ማብራሪ ሰጥተዋል፡፡ በቆይታቸውም የተለያዩ የምርምር፤የማህበረሰብ ሥራዎችን፤መሠረተ ልማቶችን እና ፕሮጀክቶችን ጎብኘተዋ።


