Our Achievements
12185
STUDENTS
854
GRADUATE
12
AWARDS
42
DEPARTMENTS
Bonga University
Vision
Bonga University aspires to be the first among the leading higher education institutions of Africa in Natural Resource management and utilization by 2030.
Mission
Fostering Community and National development through the provision of quality education enables to the production of internationally competent professionals and active engagement in demand-driven research and community services.
Latest News

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለ2017ዓ.ም 12ኛ ክፍል ማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ገለፃ/Orientation /ሰጠ።
ሰኔ 30/2017ዓ.ም መድረኩን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ነበር የከፈቱት። አክለውም ተማሪዎችን ያበረታቱ ሲሆን ፈተናውን በተረጋጋ መንፈስ በመስራት የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚገባቸው በመግለጽ መልካም ምኞታቸውንም አስተላልፈዋል። የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የሀገር ዓቀፍ ፈተና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ደጀኔ ደሱ ለተፈታኞች አጠቃላይ የሆነ ከፈተናው ጋር የተያያዙ መሠረታዊ ነጥቦችን በማንሳት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመድረኩ ላይ የተማሪዎች ዲን ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ የሁሉም ሚና የተብራራበት ሲሆን ከማን ምን ይጠበቃል የሚለውም ተበራርቷል። በጋራ እንችላለን!

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ሀገር ዓቀፉን የ12ኛ ክፍል ፈተና አስጀመሩ።
ሰኔ 23/2017 ዓ.ም. ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ የት/ት ሚኒስቴር ሚኒስትር ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢንጂነር) ጋር በመሆን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ሀገር ዓቀፉን የ12ኛ ክፍል ፈተና አስጀምረዋል። የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር)በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ት/ት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ሌሎች የፌደራል የክልል እና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል። የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ሚኒስትሩንና ልኡካቸውን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ለተፈታኞች ባስተላለፉት መልእክት እናንተን የመጣል ፍላጎት ስላለን ሳይሆን

በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለ2017ዓ.ም 12ኛ ክፍል ለመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ገለፃ /Orientation /ተሰጠ።
ሰኔ 22/2017ዓ.ም መድረኩን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የአካ/ምር/ቴክ/ሽግግርና ማህበረሰብ አ/ት ምክትል ፕሬዝዳንት ከለለው አዲሱ (ዶ/ር) ተማሪዎችን እንኳን ወደ ቤታችሁ በሰላም መጣችሁ በማለት ነበር። የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የሀገር ዓቀፍ ፈተና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ደጀኔ ደሱ ለተፈታኞች አጠቃላይ የሆነ ከፈተናው ጋር የተያያዙ መሠረታዊ ነጥቦችን በማንሳት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመድረኩ ላይ የተማሪዎች ዲን የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ የሁንሉም ሚና ከማብራራት ባሻገር ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ ፈተናውን መስራት እንደሚገባቸው በአጽንኦት ተገልጿል። በጋራ እንችላለን!

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠዉን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ሰኔ 20/2017 ዓ.ም በነገዉ ዕለት በካፋ ዞን ከሚገኙ 17ቱም መዋቅሮች 60 2ኛ ት/ቤቶች የተመደቡለትን 2240 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መቀበል እንደሚጀምር አስታውቀዋል። ፈተናዉ ከኩረጃና ተያያዥ ከሆኑ ማጭበርበሮች በጸዳ መልኩ እንዲከናወን ተማሪዎቻችን በራስ መተማመን አጎልብተዉና ተረጋግተዉ ፈተናዉን እንዲወስዱ ዩኒቨርስቲዉ የሚቻለዉን ሁሉ እንደሚያደርግ አጽንኦት ሰጥተው ገልፀዋል። በድጋሚ ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም እድል እንዲገጥማቸዉ እመኛለሁ። ደጋላ ኤርገኖ (ዶ/ር)ፕሬዝዳንት

ለ2017ዓ.ም.ሀገራዊው የ12ኛ ክፍል ፈተናን በተመለከተ ስላለው ቅድመ ዝግጅት ከተለያዩ ከውስጥና ውጭ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ።
ሰኔ 19/2017ዓ.ም***, መድረኩን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምርምር የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ከለለው አዲሱ(ዶ/ር) ከት/ት ምኒስቴር ተወክለው የመጡ የፈተና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ደጀኔ በጋራ በመሆን ነበር ወይይቱን የመሩት። በውይይቱ የዘንድሮውን ፈተና ለማከናወን ያሉ አስቻይ ሁኔታዎችን በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የስራ ክፍሎች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። የተማሪዎች አገልግሎት: የፋይናንስ: የፈተና ክፍል ዝግጅት :የትራንስፖርትና ስምሪት : እንዲሁም የፀጥታ ሀይሉ በዋናነት ማብራሪያ የሠጡ አካላት ናቸው። የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎችም የተነሱ ሲሆን የሚመለከታየው አካላትም ምላሽ ሰጥተዋል። ለዘንድሮ ፈተና በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 5631 ተማሪዎች ሲሆኑ ከሰኔ 21/2017 ዓ.ም.ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲገቡ ሰኔ 22/2017ዓ.ም ስለ

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ዘርፍ ያስተማራቸውን 918 ተማሪዎችን ለ6ኛ ጊዜ አስመረቀ።
*ሰኔ 14/2017 ዓ.ምመርሀ-ግብሩ በአባቶች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት የተጀመረ ሲሆን በመቀጠል የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) የቦርድ አመራሮችን እንዲሁም የዕለቱን የክብር እንግዳ እና ከተለያዩ መዋቅር የተጋበዙ አካላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ነበር። በመልዕክታቸው የዩኒቨርስቲው በመማር መስተማር ߹በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት እየሰራ ያለውን የተለያዩ ተግባራት አብራርተዋል። የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አቶ ማስረሻ በላቸው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ ባስተላለፉት መልእክት የበለጸጉ ሀገራት ዛሬ ለደረሱበት ምዕራፍ ያላቸው በቂ የተማረ የሰው ሀይል መሆኑን ገልጸው መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንም አውስተዋል። የትምህርት ዘመን የሚጠናቀቅ ሳይሆን የሚቀጥል በመሆኑ የዛሬ ምሩቃንም
News

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ሀገር ዓቀፉን የ12ኛ ክፍል ፈተና አስጀመሩ።
ሰኔ 23/2017 ዓ.ም. ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ የት/ት ሚኒስቴር ሚኒስትር ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ...

በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለ2017ዓ.ም 12ኛ ክፍል ለመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ገለፃ /Orientation /ተሰጠ።
ሰኔ 22/2017ዓ.ም መድረኩን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የአካ/ምር/ቴክ/ሽግግርና ማህበረሰብ አ/ት ምክትል ፕሬዝዳንት ከለለው አዲሱ...

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠዉን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ሰኔ 20/2017 ዓ.ም በነገዉ ዕለት በካፋ ዞን ከሚገኙ 17ቱም መዋቅሮች 60 2ኛ...

ለ2017ዓ.ም.ሀገራዊው የ12ኛ ክፍል ፈተናን በተመለከተ ስላለው ቅድመ ዝግጅት ከተለያዩ ከውስጥና ውጭ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ።
ሰኔ 19/2017ዓ.ም***, መድረኩን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምርምር የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የማህበረሰብ አገልግሎት...

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ዘርፍ ያስተማራቸውን 918 ተማሪዎችን ለ6ኛ ጊዜ አስመረቀ።
*ሰኔ 14/2017 ዓ.ምመርሀ-ግብሩ በአባቶች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት የተጀመረ ሲሆን በመቀጠል የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ...

The Minister of Education of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, Prof. Berhanu Nega, spoke to the Bonga University Community.
መጋቢት 11/2014 ዓ.ም የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ...

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለ2017ዓ.ም 12ኛ ክፍል ማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ገለፃ/Orientation /ሰጠ።
ሰኔ 30/2017ዓ.ም መድረኩን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ተማሪዎችን እንኳን...
About Bonga University
Producing knowledgeable, skilled, and internationally competent graduates with demand-based proportional balance of fields/disciplines promote demand-driven research focusing on technology transfer consistent with the country’s priority needs ensuring the development and dissemination of research outputs of wider impact via publications on journals, proceedings, and newsletters, as well as research symposia, workshops, seminars and public lectures, design and provide community and consultancy services that will cater to the local, and national developmental needs

Bonga University is committed to providing comprehensive student services that support academic success, personal development, and well-being. Our services include academic advising, counseling, career guidance, health care, library and ICT support, and accessible accommodation to ensure a conducive learning environment for all students.