የካቲት 17-19/2014 ዓ/ም 
በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን እና በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ  አዘጋጅነት ከሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች ጋር በግዥ አፈጻጸም ሂደት ዙሪያ የኢፌዲሪ ትምህርት ሚ/ር ሚንስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣ ክቡር አቶ ሃጂ ኢብሳ የመንግስት ግዥና ንብረት ዋና ዳይሬክተር፣ አቶ መስፍን  ነገዎ የኮንስትራክሽን ስራዎች ዋና ተቆጣጣሪ ባለስልጣን፣ የገንዘብ ሚንስተር ኃላፊዎች፣ የመንግስት ግዥ ም/ዋና ዳይሬክተሮች፣ የስታቲክስ ኤጀንሲ ዋና ኃላፊዎች፣ የደረጃ ባለስልጣን የስራ ኃላፊዎች፣ የአካባቢው ሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡

በምክክር መድረኩም ትኩረት የተደረገው በእያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ በግዥ ሂደት ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን ለማስወገድ በኦዲት አፈጻጸም ወቅት የሚታዩ የኦዲት ግኝቶችን በመለየት ጠንካራ፣ መካከለኛና በግዥ ረገድ ደከም ያለ ዩኒቨርሲቲ  መታረም ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር የተደረገ ሲሆን ለሙስና ተጋላጭ ናቸው ተብለው ከሚታሰቡ ሥራ ዘርፎች መካከል ከግዥ ቀጥሎ የኮንስትራክሽን ሥራዎች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ በኮንስትራክሽን ሥራ ቴክኒካዊና ተግባራዊ ክንውኖች በአመዛኙ ዕውቀትና ልምድ የሚጠይቁና ከፕሮጀክት ቀረጻ እስከ ውል አፈጻጸም ከዚያም ግንባታው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ያሉት ተግዳሮቶች ፈታኝ መሆናቸው ተዘርዝሯል፡፡  ግዥን በተመለከተም የዕቃው ጥራት በስፕስፊኬሽን አወጣጥ ላይ በተጠያቂነት ካልተሰራ ስፔስፊኬሽኑና የሚገባው ዕቃ የተለያየ በመሆን የኦዲት ግኝት እንዲፈጠር ምክንያት እንደሚሆን በመጠቆም በእነዚህ ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ ሀገርን ከስርቆት ነጻ ለማውጣት በቁርጠኝነት ሁሉም መረባረብ እንዳለበት በምክክር መድረኩ ተገልጿል፡፡ 

Odoo • Image and Text
Odoo • Image and Text
Odoo • Image and Text
Odoo • Image and Text