info@bongau.edu.et.com     0474524523     0474524510  

Latest News


ዩኒቨርሲቲው በካፋ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል


ቀን 02/12/2011 ዓ/ም
~~~~~~~~~~~~~~~~

ዩኒቨርሲቲው በካፋ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ ለ500 ባለድርሻ አካላት በ3ዙር የሚያልቅ የዲጂታል ሊትረሲ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፤

በሚሰጠው የስልጠና መድረክ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በዕዉቀትና በምክንያት ላይ የተመሰረተ ንቁ ማህበረሰብ ለመገንባትና መጪዋን ብሩህ ኢትዮጵያን ለማፋጠን ስልጠናዉ የአንበሳዉን ድርሻ እንደሚይዝ አበክረዉ ገልፀዋል፡፡

ሠልጣኞችም በሙሉ ልብ ምክራቸዉን መቀበላቸዉን በአዎንታ በመግለጽ በ3 ሦስት ቦታ ወደ ተከፈለዉ የስልጠና አዳራሽ በመሄድ ስልጠናዉን እየተካፈሉ ይገኛሉ፡፡

በጋራ እንችላለን!